
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ፤ ሀገር ለማተራመስ የሚጥሩ ባዕዳንን እና ባንዳዎችን ድርጊት ደግሞ የሚኮንን ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ተካሂዷል። የወረዳው ነዋሪዎች ከማለዳ ጀምሮ አደባባይ በመውጣት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት
ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመቆም የጽንፈኞችን ተልዕኮ እንታገላለን፣ ሠራዊታችን ብሔራዊ አርማችን ነው፣ ባንዳ ለሆዱ፤ መከላከያ ሠራዊታችን ለሕዝባችን ክብር እና አንድነት፣ የኅብረ-ብሄራዊነታችን ማሳያ አርማችን ነው የሚሉ እና ሌሎችንም መልዕክቶችን
ሰልፈኞቹ አስተጋብተዋል። ለሀገር ሉዓላዊነት እና አንድነት ለተሰለፈው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደጀን በመኾን የሀገር ህልውና ላይ የመጡ የባዕዳ እና ባንዳ ኀይሎችን ለመታገል ዝግጁ መኾናቸውንም ነዋሪዎቹ ጠቅሰዋል። የቃሉ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሙህዲን አሕመድ “አባቶቻችን
ጠብቀው ያስረከቡንን ሀገር ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን ኾነን በከፍታ እንጠብቃለን” ብለዋል። ሕዝቡ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ያነሳችው የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ ያገኝ ዘንድ ሕዝቡ
የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
