
ሉዓላዊነት በጀግኖቻችን መስዋዕትነት፤ ከኅብረ ብሔራዊ አንድነት እስከ ባሕር በር ባለቤትነት” በሚል መሪ መልዕክት የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ሕዝባዊ የሰላም ሰልፍ አካሂደዋል። ነዋሪዎቹ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፉ፤ የባዕዳን እና የባንዳን ዕኩይ ሴራ የሚያወግዙ መልዕክቶችን በሰልፉ ላይ አስተጋብተዋል።
የወረባቦ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አደም አሕመድ ኢትዮጵያውያን በአንድነት እና በጀግንነት የምንታወቅ፤ ለባዕዳ እና ባንዳ የጥፋት ተልዕኮ የማንበረከክ የነጻነት ቀንዲል መኾናችንን ዛሬም ለዓለም ያሳየንበት ሕዝባዊ ሰልፍ ነው ብለዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ክቡር መስዕዋትነት
እየከፈለ ዛሬም ሀገራችንን ከውጭም፣ ከውስጥም ጠላት ጠብቆ በክብር ወደ ላቀ ከፍታዋ ለምታደርገው ጉዞ ደጀንነቱን እያሳየ ይገኛል ነው ያሉት። የወረባቦ ሕዝብ ለሰላም መስፈን እና ለሕግ የበላይነት መከበር ያለውን የጸና አቋም፤ ለመከላከያ እና ለክልሉ የጸጥታ ኃይል ያለውን ድጋፍ
በአደባባይ ወጥቶ የገለጸበት ታሪካዊ ዕለት ኾኖም ተመዝግቧል ብለዋል። አሚኮ ያነጋገራቸው የሰልፉ ተሳታፊዎች በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ “ሴራ እና ባንዳነት ይፈርሳሉ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እና አንድነት ከፍ ይላሉ ብለዋል። መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች
እንደግፋለን፤ በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን የአማራን እርስት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን ለመሸጥ የሚጥር ባንዳ ነው ብለዋል።
በዕለቱ “በማይነጥፈው የመከላከያ ሠራዊታችን የጀግንነት ተጋድሎ የሀገራችንን ክብር ከፍ እናደርጋለን” የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችም
ተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
