
የመካነ ሰላም ከተማ እና የቦረና ወረዳ ነዋሪዎች የመከላከያ ሠራዊቱን የሚደግፍ እንዲሁም ሀገር ለማፍረስ የሚሠሩ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶችን ሴራ የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
በሰልፉ ላይ፦
ያላቸውን ጽኑ አቋም አሳይተዋል። በተጨማሪም መንግሥት ሕግ ለማስከበር የሚያደርገውን ጥረት በመደገፍ ከሕዝብ የተወለደውን የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉን የጸጥታ መዋቅር ሁልጊዜም እንደሚያግዙ አረጋግጠዋል። በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የመካነ ሰላም ከተማ
አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ፍቅርተ ካሳው ኢትዮጵያ በጀግኖች አባቶች መስዋዕትነት የተገነባች ታላቅ ሀገር መኾኗን ገልጸዋል። አሁንም በውስጥ እና በውጭ የተደቀኑትን ተደራራቢ ፈተናዎች በሀገር ወዳዱ ሕዝብ ጥንካሬ አልፈን ለተተኪው ትውልድ የምትመች ሀገር እየገነባን እንገኛለን
ብለዋል። የሀገርን ሉዓላዊነት እና አንድነት ለማፍረስ የሚሠሩ አካላትን ሕዝቡ አጥብቆ እየተቃወመ እና የሀገር ዘብ ለኾነው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደግሞ ደጀንነቱን እያረጋገጠ ስለመኾኑም ገልጸዋል። በሰልፉ ላይ የተገኙ የሃይማኖት አባቶች ሀገር ጸንታ እንድትቆም ሁሉም በጋራ እና በትስስር መሥራት እንዳለበትም መክረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
