አትዳፈሩት፤ ጠላት የማይሻገረው የእሳት አጥር ነውና!

22

 

አትዳፈሩት፤ እርሱ በጽናት እና በጥበብ የተገነባ የኢትዮጵያ የማይበገር ጋሻ ነው! የቀጣናው የደኅንነት ዋስትናም ነው።

እርሱ ለራሱ ነብስ እና ሥጋ አይሳሳም፤ እናት ሀገሩ ከነፍሱ ጋር የተዋሃደች፣ የመኖሩም ምስጢር እና ማረጋገጫ ቤቱ ናትና። እናት ሀገሩ ስትነካ ይከፋዋል፤ ሉዓላዊነቷ ሲደፈር ያመዋል፤ ክብሯ ኩራቱ፣ ነፃነቷ ደግሞ ግርማ ሞገሱ ነው።

ለእናት ሀገሩ ያለው ፍቅር እንደ ባሕር የሰፋ፣ እምነቱ እንደ ውቅያኖስ የጠለቀ፣ ተስፋው እንደ ሰማይ ወሰን የሌለው፤ ጀግንነቱ እንደ ተራራ የገዘፈም ነው።

ለእናት ሀገሩ ነፃነት እና ክብር ሲል “ከአንቺ በፊት እኔን!” በሚል ቃለ-መሐላ የታነጸው ይህ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ታሪኩን የጻፈው በደም እንጂ በቀለም አይደለም፤ ክብሩንም ያስጠበቀው በጽናት እንጂ በቃላት አይደለም።

ለዚህ ነው እርሱ የሀገራችን የጥንካሬ ማኅተም፣ የሕዝባችን የኩራት ምንጭ ኾኖ የሚያበራው።

ከታሪክ የወረሰውን ይህንን ድንቅ የጀግንነት ቅርስ ከዘመናዊ የጦር ሳይንስ ጋር አዋህዶ፣ ዛሬም ነገም የሀገርን ሉዓላዊነት እና የሕዝብን ሰላም ለማስጠበቅ በተጠንቀቅ ቆሟል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጥንካሬ በብዛት ብቻ ሳይኾን በውጊያ ጥበብ፣ በሥነ-ልቦና የበላይነት እና በበሰለ ወታደራዊ ሳይንስ የሚመራ መኾኑን የጦር ኀይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አንስተዋል።

ሠራዊቱ በንድፈ-ሐሳብ ብቻ ሳይኾን በተግባራዊ የሜዳ ላይ ወታደራዊ ሳይንስ፣ የድብቅ ውጊያ፣ የሳይበር ደኅንነት እና የላቀ የአመራር ክህሎት ሥልጠናዎችን በብቃት ተላብሷል።

አሁን ላይ የምድር ኀይል፣ የአየር ኀይል፣ የልዩ ኮማንዶ እና የቴክኖሎጂ ክፍሎቹ በጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን እና በከፍተኛ ቅንጅት የሚንቀሳቀሱበት ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

የሀገር ውስጥ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ እና የትጥቅ ማምረቻዎች ሠራዊቱን በቴክኖሎጂ እና በትጥቅ ራሱን ችሎ እንዲቆም በማድረግ ረገድ ትልቅ ታሪካዊ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

በመኾኑም ሠራዊቱ አሁን ላይ ከውጭም ኾነ ከውስጥ የሚቃጣን ማንኛውንም ዓይነት ትንኮሳ፣ እኩይ ሴራ እና ሀገር አፍራሽ እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማክሸፍ የሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛል።

ዛሬም እንደ ትላንቱ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀጣናው ውስጥ ታማኝ የሰላም እና ደኅንነት ምሰሶ ኾኖ በጽናት ቆሟል!።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_03_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየጣና ፎረም ለአማራ ክልል ምን ይዞ ይመጣል?
Next articleአዳኝ ክንፍ!