“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገረ መንግሥት ግንባታ ያበረከተችው አስተዋጽዖ ምትክ የለሽ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

14

 

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በ45ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል።

ባስተላለፉት መልእክትም “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ፣ በቅርስ፣ በትምህርት፣ በማኅበራዊ ኑሮ፣ በደን ጥበቃ፣ በአጠቃላይ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ያበረከተችው አስተዋጽዖ ምትክ የለሽ ነው” ብለዋል።

ይሄንን ዕምቅ ዐቅም በመጠቀም ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ለማጥፋት፣ ሰላምን ለማጽናት እና ሕዝቦችን ለማስተሳሰር ግንባር ቀደም ሚና እንደምትጫወት ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

የሃይማኖት ተቋማት መንፈሳዊነትን ኃይል አድርገው ለሀገር ግንባታ በሚያደርጉት አስተዋጽዖ ሁሉ መንግሥት አብሯቸው ለመሥራት ዝግጁ ስለመኾኑም አረጋግጠዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_03_2019_ዓ_ም

Previous article🕊️ ከመሣሪያ አፈሙዝ ወደ ጠረጴዛ – የዘመኑ የጀግንነት መገለጫ
Next articleየጣና ፎረም ለአማራ ክልል ምን ይዞ ይመጣል?