
በምዕራብ ጎጃም ዞን ከ272 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በመሸፈን ከ14 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሠራ ነው የሚገኘው።
በቆሎ፣ ጤፍ ፣ ስንዴ፣ ዳጉሳ እና በርበሬ በዞኑ ላይ የተመረቱ ዋና ዋና የሰብል ዓይነቶች ናቸው።
በዞን የደረሱ ሰብሎችን ከብክነት ለመታደግ ዘመናዊ የግብርና ማሽኖች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ።
የጃቢ ጠህናን ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አስቻለው ሞሴ በወረዳው አጠቃላይ በሰብል ከተሸፈነው ከ52 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ውስጥ ከ13 ሺህ በላይ የሚኾነው ተሠብሥቧል ብለዋል።
ወቅቱ አርሶአደሮች ዓመቱን ሙሉ የለፉበትን ምርት በተገቢው መንገድ ካልሠበሠቡ ከፍተኛ የምርት ብክነት የሚፈጠርበት ስለመኾኑም ገልጸዋል።
የደረሱ የበቆሎ፣ የስንዴ እና የጤፍ ሰብሎችን የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም እንዲሠበሠብ በርብርብ እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኀላፊ አጉማሴ አንተነህ የተከሰተው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመሠብሠብ ዘመናዊ የግብርና ማሽኖችን ጨምሮ የአርሶአደሮችን የደቦ ሥራ በማጠናከር ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
ሰብሉን በፍጥነት ለመሠብሠብ የሚያግዙ 22 ኮምባይነሮች፣ 147 ሁለገብ መውቂያ ማሽን እና 407 ሌሎች መሠብሠቢያ ማሽኖች ወደ ሥራ መግባታቸውንም ገልጸዋል።
በዞኑ እስካሁን ከ76 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት የሚኾነው ተሠብሥቧልም ነው ያሉት።
አርሶአደሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ ርብርብ በማድረግ ሰብላቸውን ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ እንዲጠብቁም አሳስበዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ፍኖተ_ሰላም #ኅዳር_04_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
