በመተማ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።

12
‎በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል። ‎የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ደረሰ አዱኛ በተለያዩ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ዛሬ የሰላም ጥሪን ተቀብለው ወደ ሰላም መግባታቸውን ገልጸዋል። የገቡት ታጣቂዎች ከዚህ በኋላ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው በሰላም እና በልማት በመሳተፍ ሕዝባቸውን መካስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
‎
‎ታጣቂዎቹ ሲሄዱበት የነበረው መንገድ ስህተት መኾኑን በመገንዘብ ወደ ሰላም መምጣቸው ተገቢ ነው ብለዋል። ‎አሁንም በጫካ ያሉ ታጣቂዎች የአማራ ሕዝብ በራሱ ልጆች እየደረሰበት ያለውን በደል በመንገዘብ እና በመጸጸት የሰላም አማራጭን መቀበል እንደለባቸው አንስተዋል።
የመተማ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ አስፋው ውበት በወረዳው በተለያየ መንገድ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች መንግሥት የሰጠውን የሰላም ጥሪ በመቀበላቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ከመተማ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በቀጣይ ከመንግሥት ጎን በመኾን ልትሠሩ ይገባል ብለዋል።
‎የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ታጣቂዎችም አሁን ያለው ትግል ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመኾን ሀገርን የማፍረስ ሂደት ነው፣ ይህን ተገንዝበን የሰላም ጥሪውን ተቀብለናል ነው ያሉት።
ጦርነት አስከፊ ነው፣ የሰው ሕይወት ይቀጥፋል፣ ንብረት ያወድማል፣ እኛም በትግሉም ያተረፍነው ይህን ነው ብለዋል። የሐሳብ ልዩነትን በውይይት በመፍታት የአካባቢያቸውን ዘላቂ ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
‎
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎
Previous article‎ሰንደቅ ዓላማ የክብር ማኅተም የነጻነት አውራ
Next articleለጠላት የሚያስፈራ፤ ለሠንደቁ የሚታመን – የኢትዮጵያ አየር ኃይል