“ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያውያን የጋራ ታሪክ የተጻፈበት የጽናት ምልክት ነው” አፈ ጉባኤ አሕመድ ሽዴ

8
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 19ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኅብረ ብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ መልዕክት እያከበረ ነው።
በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አሕመድ ሽዴ ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያውያን የጋራ ታሪክ የተጻፈበት የጽናት እና የጀግንነታችን ምልክት፣ የነጻነታችን መገለጫ ነው ብለዋል።
ምክር ቤቱ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በዓሉን በበላይነት እያስተባበረ በመምራት በዓሉን የሚያደምቁ ሁነቶችን በማደራጀት ኀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleሠንደቅ ዓላማ የአንድነት እና የነጻነት ምልክት ነው።
Next article“በኢትዮጵያዊነታችንና በጋራ የልማት ራዕያችን አንድ ነን።” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ