ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር ተወያዩ።

9

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር መክረናል ብለዋል።

‎የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በልማት ትብብር ረገድ የጋራ አቅም ያላቸውን ዘርፎች ወደ ውጤት የመቀየር ሥራዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ነው ያሉት።

‎ በኢትዮጵያ የልማት ውጥኖች እና በጋራ ፍላጎት ላይ በተመሰረቱ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል። በተግባር ላይ ለተመሰረተ ትብብር ጠንካራ ትስስር መገንባት ያለውን አስፈላጊነት በትኩረት ተመልክተናል ነው ያሉት።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_02_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ።
Next articleኢትዮጵያ ትጋቷን እና ታላቅነቷን የምትገልጥበት እድል