ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ።

8

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

‎በውይይታችንም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያለውን ትብብር ማሳደግ፣ በኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት እና ኖርዌይ ኢትዮጵያ ለምትረከበው የCOP32 ፕሬዝዳንትነት የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ መክረናል ነው ያሉት።

‎

‎ውይይታችን ሰፊ የሁለትዮሽ ትብብርን ጨምሮ በወቅታዊ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሃሳብ ልውውጥ የተደረገበት ነው። ይህም በተግባራዊ የትብብር መስኮች ወደፊት ለመራመድ እና አጋርነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር ያለንን የጋራ ፍላጎት ያንጸባረቀ ነው ብለዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_02_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያዩ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር ተወያዩ።