ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያዩ።

6

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተገናኝተን መክረናል ብለዋል። ‎ከዚህ በፊት በ ግሩፕ (G20) ጉባኤ ወቅት ባካሄድነው የሁለትዮሽ ስብሰባችን ወቅት የተደረጉ ውይይቶችን ተግባራዊነት የተመለከተ ውይይት አድርገናል ነው ያሉት።

‎‎ በዋና ዋና ዓለም አቀፍ የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች፣ በቀጣናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች እና በጋራ ፍላጎቶችን በውይይታችን ተመልክተናል ነው ያሉት።

ይህም ፊንላንድ ኢትዮጵያ የምትረከበውን የCOP32 ፕሬዝዳንትነት ድጋፍ ጨምሮ የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን ዘርፎች ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት የሰጠንበት ነው ብለዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_02_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበቀይ ባሕር የምትፈለገው ኢትዮጵያ
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ።