ሠንደቅ ዓላማ የአንድነት እና የነጻነት ምልክት ነው።

5
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት “ሠንደቅ ዓላማችን ለኅብረ ብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው።
በክብረ በዓሉ የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አሥተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር)ን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀዩ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያውያን የአንድነት፣ የጀግንነት፣ የነጻነት እና የአሸናፊነት ምልክት ነው። ኢትዮጵያውያን ለሠንደቅ ዓላማቸው ክብር እና ለሀገራቸው ፍቅር ክቡር መስዋዕትነት ሲከፍሉ ኖረዋል።
በሠንደቅ ዓላማቸው ጥላ ሥር ተሰባስበው በአንድነት ጸንተዋል፤ የሀገራቸውን ሉዓላዊነት እና ነጻነት ለዘመናት አጽንተው ኖረዋል። ዛሬም ለሠንደቅ ዓላማቸው እና ለሀገራቸው በአንድነት ቆመዋል።
ሠንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያውያን የአርበኝነት እና የማንነት መገለጫ ነው።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየጥላቻ ንግግር ምንድን ነው?
Next article“ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያውያን የጋራ ታሪክ የተጻፈበት የጽናት ምልክት ነው” አፈ ጉባኤ አሕመድ ሽዴ