
የሐረር ከተማን ዕድገት የሚያፋጥኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የሐረሪ ክልል አስታውቋል።
የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጄክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የሐረር ከተማን ዕድገት የሚያፋጥኑ እና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትኾን የሚያስችሉ ዘርፈ-ብዙ የልማት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
የልማት ፕሮጄክቶቹ የማኅበረሰቡን ፍላጎት ማዕከል አድርገው እየተከናወኑ የሚገኙ ናቸው። ለዜጎች ዘላቂ ጥቅም እንዲያስገኙ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል። እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ከተማዋን ለኑሮ የተመቸች እና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።
በክልሉ በኮሪደር ልማት የተመዘገቡ ውጤቶችን ከማስቀጠል ባለፈ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ የሕዝቡን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች የሚመልሱ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
#የመደመር_መንግሥት
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ፣ #ታላቅ_ርዕይ 🇪🇹🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
