
በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ መኾኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማዕከላዊ መጋዘን የተጫነ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ አፋር ክልል በመጓጓዝ ላይ መኾኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።
ለተፈጥሮ እና ሠው ሠራሽ አደጋዎች ክልሎች በራሳቸው አቅም ምላሽ ለመስጠት እየተረባረቡ መኾኑን አንስቷል። ኮሚሽኑም የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብሏል።
የአፋር ክልል በራሱ አቅም የሚያደርገው ድጋፍ እና ክትትል እንደተጠበቀ ኾኖ ኮሚሽኑም የቅርብ ድጋፍ እና ክትትል እያደረገ መኾኑን ገልጿል።
በዚህም ከአዳማ የመጠባበቂያ መጋዘን ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ የአፋር ክልል ተንቀሳቅሰዋል ነው የተባለው።
#የመደመር_መንግሥት
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ፣ #ታላቅ_ርዕይ 🇪🇹🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
