
በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ተገኝተዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ የጎበኙት የአጼ ሠርጸ ድንግል ልዩ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእድሳት እና የጥገና ሥራ፣ የባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ አልቤስት ትሬዲንግ የሆቴል ግንባታ ፕሮጄክት፣ ዓለማየሁ ካሳ ደረሰ የሆቴል ፕሮጄክት፣ የበላይነህ ክንዴ ሂልተን ሆቴል ፕሮጄክት እና የፎር ፖይንት ባይ ሸራተን ባሕር ዳር ጣና ሆቴል ፕሮጄክትን ነው።
በጣና እያጌጠች፣ በዓባይ እየደመቀች የኖረችው ባሕር ዳር ከተማ አሁን ደግሞ በልማት ሥራዎች እየተዋበች ነው። ዛሬ የተጎበኙት የልማት ሥራዎች የባሕር ዳር ከተማን ዘመናዊነት የሚጨምሩ እና እድገቷን ከፍ የሚያደርጉ ናቸው።
ለወትሮው የቱሪዝም መዳረሻ የኾነችው ባሕር ዳር ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ የሆቴል ግንባታዎች ሲጠናቀቁ የቱሪዝም እንቅስቃሴዋን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ። የከተማዋን ገጽታም ከፍ ያደርጋሉ። ተፈጥሮ እና የልማት ሥራዎች የተዋሃዱባት ከተማዋ አሁን ላይ በጥሩ የልማት ደረጃ ላይ ናት።
ባሕር ዳር ለቱሪዝም፣ ለአምራች እንዱስትሪ፣ ለትምህርት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች የተመቸች ከተማ ናት።
የመደመር_መንግሥት
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ፣ #ታላቅ_ርዕይ 🇪🇹🇪🇹
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#ባሕር_ዳር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
