የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ዕውቅና ሰጠ።

7

የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር በ2018 ዓ.ም በክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ለታታሪ መምህራን የምሥጋና፣ የዕውቅና እና የሽልማት መርሐግብር አካሂዷል።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በሪሁን መንግሥቱ መምህራን ትውልድን የሚገነቡ የሕዝብ ባለውለታዎች መኾናቸውን ገልጸዋል።

የተጀመረውን የትምህርት ጥራት የማስከበር ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ እየበሩ አዕምሮ ለተማሪዎች እና መምህራን ዕውቅና መስጠት ለቀጣዩ ትውልድ የሞራል ስንቅ እንደሚኾን ገልጸዋል።

በክልል እና በሀገር አቀፍ ፈተናዎች የተሻለ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች በአይነት እና በገንዘብ የተደረገው ማበረታቻ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። በቀጣይም ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የበቁ እንዲኾኑ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን አስረድተዋል።

ዕውቅና የተሰጣቸው ተማሪ ትህትና ክንዱ እና ተማሪ ሃይማኖት ደጀን ለስኬታቸው የግል ጥረታቸው፣ የወላጆች፣ የመምህራን ድጋፍ እና ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እንደረዳቸው ገልጸዋል። ተተኪ ተማሪዎችም የነሱን አርዓያ ተከትለው ጠንክረው እንዲማሩ መክረዋል።

የተማሪ ትህትና ክንዱ ወላጅ ሲስተር አገሬ ታረቀኝ ልጃቸውን ከቤት ሥራ ጫና ነፃ በማድረግ እና አስፈላጊውን ቁሳቁስ በማሟላት እንደደገፏት ገልጸዋል። ሌሎች ወላጆችም ለልጆቻቸው የጥናት ጊዜ በማመቻቸት ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ እና ማኅበራዊ ሚዲያን በአግባቡ እንዲጠቀሙ አስገንዝበዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ደብረታቦር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፡ ተክለብርሃን ፈንታ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበክልል ፍርድ ቤቶች በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የተቀራረበ ደረጃ እንዲኖር ተሠርቷል።
Next articleሐቅን መርህ በማድረግ ሉዓላዊነትን የመጠበቅ ተጋድሎ!