‎ባለ ጉዳዮች የፍትሕ አገልግሎትን በቪዲዮ ኮንፈረንስ እያገኙ ነው።

1

‎
‎ሀገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች ውይይት በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። በመርሐ ግብሩ የፌዴራል እና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች ተገኝተዋል። ፕሬዝዳንቶቹ በሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች የጋራ የለውጥ ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው።
‎
‎በመርሐ ግብሩ የተገኙት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ የተቋቋመበት ዓላማ በሕግ የመተርጎም ሚና የተለያዩ አተረጓጎሞች እና ሥርዓቶች ኑረው በሀገሪቱ አመቺ ያልኾነ የፍርድ ሂደት እንዳይኖር የመከላከል ዓላማ የያዘ ነው ብለዋል።
‎
‎ተመሳሳይ የሕግ አተረጓጎም እና አተገባበር እንዲኖር ለማስቻል ያለመ መኾኑን ተናግረዋል። ሀገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚ ከተቋቋመ በኋላ በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገቡንም ገልጸዋል። ለውጡ ተስፋ ሰጭ እና አበረታች መኾኑን ነው ያነሱት።
‎
‎የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና የጎደሉትን ለመሙላት ውይይት ይደረጋል ነው ያሉት። የለውጥ ፍኖተ ካርታውንም በጋራ በመናበብ ሥራ ላይ ማዋል ተችሏልም ብለዋል። በዚህም በዲጂታላይዜሽን ሂደት በክልሎች የነበረውን የተራራቀ አፈጻጸም ማቀራረብ ተችሏል ነው ያሉት።
‎
‎የተገኘው ውጤት እርካታን የፈጠረ፤ የፍርድ ቤቶችን የፍትሕ ተደራሽነት ያረጋገጠ፤ የውሳኔዎችን ጥራት ያሻሻለ መኾኑንም ተናግረዋል። በክልሎች የተቀናጀ የጉዳዮች ፍሰት መረጃ አሥተዳደር ሥርዓት በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባም አንስተዋል።
‎
‎ባለ ጉዳዮች የፍትሕ አገልግሎትን በቪዲዮ ኮንፈረንስ በሁሉም ክልሎች አገልግሎት እያገኙ ነው ብለዋል። የኢ ፋይሊንግ አገልግሎትን ለማስፋት ጥረት እየተደረገ መኾኑንም አንስተዋል።
‎
‎የተጀመሩ ውጤቶችን በትኩረት ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል። በቀጣይ ሦሥት ዓመታት ሊተገበር የሚችል ፍኖተ ካርታ በውይይቱ እንደሚጸድቅም አመላክተዋል።
‎
‎በመድረኩ የኢትዮጵያ የዳኝነት አካላት በሚሠሩት የለውጥ ሥራ የሚጓዙበትን አቅጣጫ መንገድ የምንቀይስበት ነው ብለዋል።
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም
‎
‎ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መመረቅ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው።
Next articleበክልል ፍርድ ቤቶች በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የተቀራረበ ደረጃ እንዲኖር ተሠርቷል።