የብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መመረቅ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው።

7

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መመረቅ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው።
‎
‎በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጋርነት የተቋቋመው ይህ ማጣሪያ ፋብሪካ፤ የማዕድን ዘርፉን ለማጠናከር እና በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት ለመጨመር የተያዘውን ዓላማ ለማሳካት ትልቅ እመርታ ነው።

‎የማዕድን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቅድሚያ የሚሰጠው አምራች ዘርፍ ነው። በተለይም ወርቅ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። ይህ ተነሳሽነት የሀገሪቱን ሀብቶች ከሀገር ውስጥ ማቀነባበሪያ፣ ከኢንዱስትሪ አቅም እና ዘላቂ እሴት ፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የመደመር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
‎
‎ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ነው። የወርቅ ጥራትን ለመለካት፣ ለማንጠር እና ለውጭ ገበያ ዝግጁ ወደኾኑ ንጹሕ ወርቆች ለመቀየር፣ በተለያዩ የጥራት ደረጃዎች የተሰናዱ የወርቅ እና የብር ጡቦች ለማምረት ታስቦ የተገነባ ነው።
‎
‎ማጣሪያ ፋብሪካው በውድ ማዕድናት ማጣራትና ማምረት ረገድ ኢትዮጵያን የቀጣናው ማዕከል ለማድረግ መሠረት የሚጥል ነው። የወርቅ ዋጋ አተማመን ላይ ግልጽነትን፣ የጥራት ማረጋገጫን እና እምነትን ያሳድጋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ላቀ የሀገር ውስጥ እሴት፣ ጠንካራ የኢንዱስትሪ አቅም፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ ገበያዎች ሰፊ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚረዳ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው።
‎
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው
‎ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ግልጽ የኾነ ትልቅ ርዕይ ያነገበ ነው። ይህም ጥሬ ማዕድናትን ዝም ብሎ ከመቆፈር ባለፈ፣ ማቀነባበር፣ ማምረት እና በሀገር ውስጥ የላቀ እሴት መፍጠር ላይ የሚያተኩር ነው።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ጎንደር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበትግራይ ክልል ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እንዲገቡ መንግሥት ጥሪ አቀረበ።
Next article‎ባለ ጉዳዮች የፍትሕ አገልግሎትን በቪዲዮ ኮንፈረንስ እያገኙ ነው።