
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። መንግሥት ዋና ዓላማው የወጣቱን ሕይወት ማትረፍ መኾኑን የገለጹት የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የዲሞቢላይዜሽን እና ተሃድሶ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው ናቸው።
በአሁኑ ጊዜ በትግራይ መከላከያ የሌለበት አካባቢ የሌለ በመኾኑ ታጣቂዎች ለመከላከያ በሰላም ትጥቃቸውን በማስረከብ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ማዕከልም የሰላም ከለላ እና ሥልጠና ያገኛሉ ብለዋል።
ወንጀለኛው ቡድን በቅርቡ ጦርነት በመቀስቃስ ይህን ሥራ ማስተጓጎሉን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ በትግራይ ብቻ ከዚህ በፊት 63 ሺህ ታጣቂዎች በተሃድሶ ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቅለዋል ነው ያሉት።
ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያ በማብራሪያቸው መንግሥት በክልሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን ቢቆይም፥ የሕወሃት ቡድን ለጦርነቱ እጅግ የከፋ አካሔድን እየተከተለ በመኾኑ የትግራይ ወጣት እራሱን ከጦርነት ለማትረፍ ወደ ተሀድሶ ማዕከል ለመቀላቀል እንዲችል ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ገልጸዋል።
መንግሥትን የሰላም ጥሪን ተቀብለው ለሚመጡ ታጣቂዎች በሩ ክፍት መኾኑንም አረጋግጠዋል። ሰላም ፈላጊ ለኾኑ ታጣቂዎች በማይጨው እና መኾኒ ከተሞች፣ በመቀሌ፥ በአክሱም፣ በሽሬ፣ በአዲግራት እና በውቅሮ ከተሞች የቅበላ ማዕከላት መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል።
መንግሥት ከአጋዥ አካላት ጋር በመተባበር ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ከ92 ሺህ በላይ ታጣቂዎችን በተሃድሶ ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ብለዋል።
15 ሺህ 200 በአማራ ክልል፣ 63 ሺህ 800 በትግራይ እና 11 ሺህ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በተሃድሶ ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ መኾናቸውን ገልጸዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#አዲስ_አበባ #መስከረም_30_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
