“ሠራዊታችን የጦር ሰባቂዎችን ሕልም ማምከኑን ይቀጥላል” ሌትናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ

43

የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌትናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ከተሰማሩ የጦር ክፍሎች መሪዎች እና ከአንድ ሬጅመንት አባላት ጋር የቀጣይ ግዳጅ ሰጥተዋል፡፡

በንግግራቸውም “እኛ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የምናስከብር ሠራዊት ነን ብለዋል፡፡ ለኛ ተዋግቶ ማሸነፍ የምንታወቅበት ነው፤ እኛ ለኢትዮጵያ የምንከፍለው መስዋዕትነት ክቡር ነው፤ አባቶቻችን ያቆዩልንን ሀገር የምናስቀጥል ጀግኖች ነን” ብለዋል። በየጫካው የተደበቀውን ጽንፈኛ አሳድዶ በመመንጠር ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

እነዚህ የምንዋጋቸው ጽንፈኛ ባንዳዎች እና ታሪካዊ ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ህልውና እና የሕዝባችንን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል የሚያደርሱትን የጥፋት ተግባር ለማስወገድ እና ሰላም ለማስጠበቅ ከፊት የተሰለፍን ጀግኖች ነን ብለዋል፡፡

ሠራዊቱ በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል ሸኔን እና አልሸባብን፤ በጎጃም እና በደቡብ ጎንደር ደግሞ ጽንፈኛን በማሽመድመድ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ እንደሚኝም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለማፍረስ አስበው የሚሠሩ ተላላኪዎች ላይ እያሳረፍነው ያለው ብርቱ ክንድ ያስደነገጣቸው ባዕዳን ያደገች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት አይፈልጉም ነው ያሉት፡፡ ኢትዮጵያን እንደ በፊቱ ቀጥታ ከመውረር ይልቅ የኛኑ ባንዳዎች በመመልመል፣ በማሠልጠን ፣ በማስታጠቅ እንዲሁም በማሠማራት እያወኳት ይገኛሉ ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የሚዋጉን ጽንፈኞች ታሪካዊ ጠላቶቻችን የሚጋልቧቸው የጥፋት መልዕክተኞች ናቸው ብለዋል፡፡ እነዚህ ተላላኪ ባንዳዎችን ለመምታት የምናደርገውን ሕግ የማስከበር ተልዕኮ በማፋጠን የጠላቶቻችንን ምኞት ማምከን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በሀገራችን ሰላም፣ እድገት እና ደኅንነት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች በልማታችን እና በእድገታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚፈጥሩ ተገንዝበን በእያንዳንዱ የውጊያ አውድ ላይ የምናደርገውን ስምሪት በአጭር ጊዜ በድል ማጠናቀቅ ይገባናል ነው ያሉት። ዘገባው የምሥራቅ ዕዝ ነው።

#የመደመር_መንግሥት

#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ፣ #ታላቅ_ርዕይ 🇪🇹🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_29_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article‎”የኢትዮጵያ ጥንካሬ እና የማይበገረው ሕዝባዊ አንድነት”
Next article‎🌾”እንደ ዘንድሮ ሰብል በቅሎ አያውቅም” አርሶ አደር