ታራሚዎች በይቅርታ እና በክስ መቋረጥ መፈታታቸው ከሰብዓዊ መብት አኳያ አወንታዊ ነው።

4

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዓመታዊ ሪፖርቱን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ከ729 በላይ የሕግ ታራሚዎች መፈታታቸውን እንደ አዎንታዊ እርምጃ የጠቀሰው ኮሚሽኑ፣ የሰብዓዊ መብቶችን ጥበቃ ለማጠናከር ተጠያቂነት እና ሰላማዊ የግጭት አፈታት እንዲተገበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ከ729 በላይ የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ እና በክስ መቋረጥ መፈታታቸውንም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ብረሃኑ አዴሎ ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ከሰኔ 2017 እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውን አምስተኛ ዓመታዊ ሪፖርቱን ሲያቀርብ ኮሚሽኑ 98 ማረሚያ ቤቶች፣ 649 የፖሊስ ጣቢያዎች መጎብኘታቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ የድምጽ አሰጣጥ እና ከፍተኛ ተሳትፎ መመዝገቡ እንደ አዎንታዊ ጉዳይ የጠቀሱት ኮሚሽነር ብርሃኑ የኢንተርኔት መቆራረጥ እና ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ያልኾኑ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ክፍተቶች እንደነበሩ ሪፖርቱ አመላክቷል።

ኢሰመኮ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እንዲሁም በግጭቶች የሚጎዱ ዜጎችን ጥበቃ የሚሰጡ ሕጎች ተግባራዊ እንዲኾኑ ምክረ ሐሳቦችን አቅርቧል።

ኢሰመኮ በሪፖርቱ ያነሳቸው ጉዳዮች የሰብዓዊ መብቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ሥራ እንደሚያስፈልግም ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ አሳስበዋል።

ግጭቶችን በሰላም መፍታት፣ ለጥሰቶች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እና የተጎጂዎችን መብት መጠበቅ ደግሞ የሁሉንም ተዋናዮች ትኩረት ይሻሉ ብለዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#አዲስ_አበባ #መስከረም_29_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦አየለ መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleለሰብል ሥብሠባ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሰው ኃይል እንደሚፈልግ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስታወቀ።
Next article‎”የኢትዮጵያ ጥንካሬ እና የማይበገረው ሕዝባዊ አንድነት”