የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛው ዓመታዊ የዳኞች ጉባኤ የማጠቃለያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

11
በመርሐ ግብሩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ጉባኤው ከመስከረም 20/2019 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ ነው የቆዬው። በጉባኤው የክልሉን ዳኞች አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ የፓናል ውይይቶች፤ ሥልጠናዎች እና ሌሎች መርሐ ግብሮች ተከናውነዋል፡፡
ተምሳሌት የኾነ ፍርድ ቤት ለመገንባት ርዕይ ይዞ እየሠራ የሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዲጂታላይዜሽንን በመተግበር ፈጣን እና ቀልጣ አገልግሎት እየሠጠ ነው።
ዳኞች ሙያዊ ሥነ ምግባርን አክብረው እንዲሠሩ እና አቅማቸውን እንዲያጎለብቱም እየተሠራ ነው።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleጠላትን ደጋግሞ እንዲያስብ ያስገደደው የአየር ኀይል የቴክኖሎጂ አቅም
Next articleከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር – የኢትዮጵያ የማይናወጥ ሉዓላዊነት እና የጂኦ-ፖለቲካ ድል!