የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት፦

6
‎በዛሬው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት የቀረቡትን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን አጽድቋል።
‎
‎ሹመት የምንዝናናበት ሳይሆን የምንፈጋበት፣ የምንሰራበት፣ ኢትዮጵያን ለማጽናት፣ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ፣ ኢትዮጵያን ወደ ስልጣኔ ጉዞ ለማስኬድ ከፍተኛ ጥረት የሚደረግበት መስክና የሀገር ትልቅ አደራ ነው።
‎
‎በሚቀጥሉት ዓመታት ኢትዮጵያ በውሳኔዋ ሉዓላዊ፣ በልዩነት ውስጥ የተሳሰረች፣ እሴት በመፍጠርና ጠብቆ በማቆየት ረገድ ምርታማ፣ ቀጣናዊና
አህጉራዊ መልህቅ በመሆን የምትመራ፣ እንዲሁም ለቀጣዩ ትውልድ በምታሸጋግራቸው አቅሞች ጸንታ እንድትቀጥል ሰፊ ስራ ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት ይህንን እውን ለማድረግ ቁርጠኛ ነው!
Previous articleየአውሮፓ ኅብረት አዲስ ለተመሠረተው የመደመር መንግሥት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።