
አቶ ተመስገን ጥሩነህ የትምህርት ዝግጅታቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ አላቸው። በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ የሕዝብ አሥተዳደር ያላቸው ናቸው።
በልጅነታቸው የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ተቀላቅለው እስከ ሻለቃ መሪነት ድረስ አገልግለዋል። ከዛም የኢንሳ፣ የብሔራዊ ደኅንነት ዋና ኀላፊ ኾነው አገልግለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ በመኾን ለኢትዮጵያ ደኅንነት አስፈላጊ ስልታዊ ሰነዶች በማዘጋጀት ከፍተኛ ሚና ያላቸውም ናቸው።
በቴክኖሎጂ ረገድ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመዘገበ ያለውን ቴክኖሎጂ ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በመምራት ያላቸውን የትምህርት ዝግጅት ታሳቢ በማድረግ አብዛኛውን ኢትዮጵያ ላይ የሚሠራውን (ሞባይል ባንኪንግ፣ ዲጅታል መታወቂያ፣ የመሰሉ ጉዳዮች) በቅርበት መርተዋል።
ከሕዝብ አሥተዳደር አንጻር በአማራ ክልል የመንገድ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እና የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኾነው አገልግለዋል።
ላለፉት ጥቂት ዓመታት ደግሞ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው አገልግለዋል። በዚህም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሕዝባቸውን ለማገልገል ባላቸው ልምድ፣ ታማኝነት፣ ቁርጠኝነት እና ሕዝባቸውን ለማገልገል ያላቸውን ልምምድ ታሳቢ በማድረግ በድጋሜ ለኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት በእጩነት ቀርበዋል።
#አሚኮ-ባሕርዳር-መስከረም 28/2019ዓ.ም
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
