
በሐረሪ ክልል በየደረጃው የሚገኘው አመራር በተደመረ አቅም የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠል እና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ሊሠራ እንደሚገባ የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በክልሉ ለተሾሙ አዳዲስ የሥራ ኀላፊዎች የሥራ መመሪያ እና አቅጣጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በክልሉ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች አበረታች እመርታ ያሳዩ እና ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው።
ይህን ስኬት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲቻልም መሪው ሕዝቡን በማስተባበር በታማኝነት፣ በትጋት እና በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም ሌብነትን፣ ሙስናን እና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል የሕዝብን እምነት ማትረፍ እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ያሳሰቡት ርእሰ መሥተዳድሩ በተቋማት የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ መጓደሎችን በማረም አሠራርን ማዘመን እና በጥሩ ሥነ-ምግባር ማገልገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አስከትለውም በመደመር እሳቤ በመመራት የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ የልማት ሥራዎችን ይበልጥ ማስፋት እና ለላቀ ስኬት ማብቃት እንደሚገባም አሳስበዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_27_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
