ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሏቸው የሁለትዮሽ ትብብር መስኮች ዙሪያ ዛሬ ከናይጄሪያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሴናተር ካሺም ሼቲማ ጋር ተወያይተናል።

15
በውይይታችን ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ትብብርና የልምድ ልውውጥ ላይ በስፋት መክረናል።
ናይጄሪያ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የተገኘውን ተጨባጭ ስኬት በመገንዘብ የኢትዮጵያን ልምድ ለመቅሰም በልዑካኗ በኩል ላደረገችው ጉብኝት ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ክቡር ምክትል ፕሬዝዳንት ሴናተር ካሺም ሼቲማ በሀገራቸው የሥርዓተ ምግብን ለማሻሻል የሚያሳዩት ቁርጠኝነትም ለአህጉራችን አርአያ የሚሆን ነው።
ኢትዮጵያና ናይጄሪያ በስትራቴጂካዊ አጋርነት የተሣሠሩ ሲሆን፣ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሕዝብና የኢኮኖሚ አቅም በተቀናጀ መልኩ መሠማራት አፍሪካን በተሻለ መንገድ ለመቅረጽ ያለውን ዐቅም በይበልጥ ያጎላል።
ኢትዮጵያ ለናይጄሪያ የዲፕሎማቲክና የሰርቪስ ፓስፖርት አሠራሮችን ማሻሻሏን እንዲሁም የዲፕሎማቲክና የሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ የናይጄሪያ ዜጎች የቪዛ ነጻ የጉዞ ሥርዓትን በሥራ ላይ አውላለች። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሰዎች ለሰዎች ግንኙነትና የዲፕሎማሲያዊ ትሥሥር የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችል ዐቅም ነው።
በኢንቨስትመንት ዘርፍም አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ ልማት ውስጥ እያበረከቱ ያሉትን ጉልህ አስተዋጽዖ አንስተናል። በተጨማሪም ሌሎች የናይጄሪያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ሊያደርጉ ስለሚችሉባቸው ዕድሎችና ተወያይተናል።
Previous articleየክልሉ ፍርድ ቤቶች የዲጂታል መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ኾነዋል።
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ነው።