
በሐረሪ ክልል 5 ሺህ ሔክታር መሬት የሚሸፍን የበጋ መስኖ ልማት የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በተገኙበት ተጀምሯል።
በማስጀመሪያው ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኀላፊ ሮዛ ዑመር በተያዘው ዓመት 5 ሺህ ሔክታር መሬት በበጋ መስኖ በማልማት እስከ 1 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውቀዋል።
በክልሉ ሁሉም የገጠር ወረዳዎች የበጋ መስኖ ልማቱ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል።
በዚህም የተለያዩ አትክልት፣ ፍራፍሬና ሰብሎችን ለማምረት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ለበጋ መስኖ ልማቱ አስፈላጊ የሆኑ የዘር፣ የማዳበሪያ፣ እና የውኃ አማራጭ አቅርቦትን ማሳደጊያ ግብአቶች ለአርሶ አደሮች ማቅረብ መቻሉንም ገልጸዋል።
በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና ከተረጂነት በመውጣት የአርሶ አደሮችን ሕይወት ለማሻሻል እና የምርቶች የገበያ አቅርቦትን የመጨመር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስገንዝበዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_28_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
