“የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሐዝ እንዲወርድ በትኩረት ይሠራል” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

7
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባ ተካሂዷል። በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሠባ የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም ኢትዮጵያ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በአገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛ እመርታ ለማስመዝገብ እየሠራች መኾኗን ገልጸዋል።
በቀጣይ:-
✍️የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት 65 በመቶ ማድረስ እና የንጹሕ መጠጥ ውኃ ሽፋን ላይ በስፋት ይሠራል ብለዋል።
✍️የጤና መድኅን ሽፋን ወደ 85 በመቶ እንዲያድግ ይደረገል።
✍️የደን ሽፋን አሁን ካለበት 26 በመቶ ከፍ እንዲል፤
✍️የመሶብ አንድ ማዕከላት እንዲበራከቱ፤
✍️የተማሪዎች ምገባ ሽፋንም 70 በመቶ እንዲደርስ፤
✍️የፍትሕ ዘርፉ የበለጠ እንዲዘምን ይደረጋል ብለዋል።
👉 በሀገራዊ ምክክሩ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦች ወደ ተግባር እንዲገቡ ይደረጋልም ብለዋል።
✍️አስተማማኝ የባሕር በር መሻታችን በጋራ ጥቅም፤ ሰጥቶ በመቀበል እና በሰላማዊ መንገድ እውን እንዲኾን ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።
✍️የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር ወደ 9 ነጥበ 62 በመቶ ከፍ እንዲል እና “የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሐዝ እንዲወርድ
በትኩረት እንደሚሠራም” አንስተዋል። የታክስ ገቢን ከፍ ማድረግ የትኩረት አቅጣጫ እንደኾነ ነው የተናገሩት። የኢኮኖሚ እድገታችን 10 ነጥብ 1 በመቶ እንዲኾን በትጋት የሚሠራ ይኾናል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article‎የ2019 ዓመት ዕቅድ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች የሚያስከብር ነው።
Next articleበጥልቅ ሃሳብ መመራት እና ችግሮችን አስቀድሞ መለየት የኢትዮጵያ ብሩህ መንገድ አመላካቾች ናቸው።