
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባ ተካሂዷል። በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሠባ የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ንግግር አድርገዋል።
በሰባት ዓመት ውስጥ 1 ቢሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት መጨመር ታላቅ እመርታ ብቻ ሳይኾን ታላቅ ልዕልና ስለኾነ ሊሞገስ ይገባዋል ነው ያሉት።
ውጤቱ የበርካታ ሰዎች ሃሳብ፣ ዕውቀት፣ ላብ እና ጉልበትን የጠየቀ መኾኑንም ተናግረዋል። በዚህ የላቀ ውጤት ለተጉ በሙሉ ምስጋናም አቅርበዋል።
ውጤቱ በውጫዊ እና በውስጣዊ ጫና እያለፍን የተመዘገበ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ያቀደችው እድገት ፈተናዎችን የሚቋቋም ብቻ ሳይኾን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ሁለገብ ጥረት ተጨማሪ ብልሃት እና አቅም መኾን መቻሉ ነው ብለዋል።
መንግሥት የኢትዮጵያን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ሁሉንም የጥንካሬ አቅሞች በማደራጀት የሀገርን እድገት እና ብልጽግና ለማፋጠን የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
