
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ሥብሠባ እየተካሄደ ነው። በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሠባ የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ንግግር አድርገዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የሕዝብ ምክርቤት የመንግሥት ሥልጣን መሠረቱ ሰፊው ሕዝብ መኾኑ የሚረጋገጥበት ሕያው ማሕተም እና ምስክር ነው ብለዋል።
የምክር ቤት አባላት የሚያከናውኗቸው ተግባራት እና የሚደነግጓቸው ሕጎች በዘመናዊዋ ኢትዮጵያ የሥልጣን ፍኖት የተጣለባቸው ኀላፊነት ከፍ ያለ መኾኑን አስገንዝበዋል።
የምክር ቤት አባላት “የመረጣችሁ ሕዝብ ከእምነት ጋር ታላቅ አደራ ጥሎባችኋል” ነው ያሉት። ይህንንም በጥበብ እና በማስተዋል መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የምክርቤቱ ቀዳሚ ትኩረት መልካም አሥተዳደርን የሚያዘምን፣ ኢኮኖሚን ከፍ የሚያደርግ፣ ትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ይበልጥ የሚያስፋፋ፣ ምርት እና ምርታማነትን የሚያሳድግ፣ የኑሮ ውድነትን የሚገራ፣ የመሠረተ ልማቶችን የሚዘረጋ፣ የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት የሚያጸና ሊኾን ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
