“ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ የላትም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

17
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ሥብሥባውን እያካሄደ ነው።
በምክርቤቱም ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ተመርጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ያሳለፍነው ምርጫ ከማንኛውም ምርጫ በተለየ በፈተናዎች የታጀበ እንደነበር አንስተዋል።
የምርጫ ሂደቱ የዴሞክራሲ ባሕል እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ሕዝቡ ሕልውናውን ለማስቀጠል ችግሮችን ተቋቁሞ መምረጡንም ተናግረዋል።
ማንኛውም ፓርቲ በምርጫ አሸናፊ እና ተሸናፊ ሊኾን ይችላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” ሲሉ አረጋግጠዋል።
እንደ ሀገር የሚጠብቀንን ፈተና መራመድ የምንችለው እንደ ወንድማማች ተያይዘን እኩል መራመድ ስንችል ብቻ ነው ብለዋል።
ለዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዋጋ ሰጥተው በሕጋዊ ምርጫ እምነት ጥለው በምርጫ እምነታቸውን ለሰጡ 54 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ምሥጋናም አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ።
Next article“በአንድ እንቅፋት አንዴ መመታት ተፈጥሯዊ ቢኾንም ደጋግሞ መመታት ግን የጤና አይደለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)