የማኅበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድኅን አገልግሎትን ማጠናከር የመሪዎች ቁልፍ ተግባር ሊኾን ይገባል።

10

 

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የማኅበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን ፕሮግራም የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ግምገማ ዞናዊ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የየወረዳዎቹ የጤና ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች የአፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።

የኩታበር ወረዳ የጤና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብዱ እሸቱ በ2018 በጀት ዓመት የወረዳው አፈጻጸም 97 በመቶ እንደነበር ጠቁመዋል።

በያዘነው በጀት ዓመትም አፈጻጸሙ ከ50 በመቶ በላይ መድረሱን እና ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡን አስታውቀዋል።

የአርጎባ ወረዳ የጤና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኑሩ ይማም በኅብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ እና የመድኃኒት እጥረት ችግሮችን በመፍታታቸው ባለፈው በጀት ዓመት ከዕቅድ በላይ መፈጸማቸውን ገልጸዋል። ዘንድሮም የተሻለ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየሠሩ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ኀላፊ ጌታቸው በለጠ በ2018 በጀት ዓመት 812 ሚሊዮን ብር ከጤና መድን መዋጮ መሠብሠቡን ተናግረዋል። 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የሕክምና አገልግሎት አግኝተዋል።

የክትትል እና ድጋፍ ሥራዎችን ለማሳለጥ የጤና ተቋማትን በዲጂታል የማስተሳሰር ሥራ እየተከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት።

በ2019 በጀት ዓመትም ዘላቂ የፋይናንስ አቅርቦትን በማሳደግ ፍትሐዊ እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷል። ለዚህም ከ904 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሠብሠብ እየተሠራ ነው።

የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኛው ማኅበረሰቡ ፕሮግራሙን ባሕሉ ማድረጉን ጠቁመዋል። አሁን ዋናው ትኩረት ሊኾን የሚገባው የአገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን፣ ግልጽነት ባለው መልኩ ተቋማዊ ማድረግ እና ጥራቱን ማረጋገጥ እንደኾነ አብራርተዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን ለማኅበረሰባችን ጤና መጠበቅ ዋስትና የኾነውን የማኅበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድኅን አገልግሎትን መሪው ቁልፍ ተግባር አድርጎ ሊፈጽመው ይገባል ብለዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ደሴ #ጥቅምት_25_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፡ መሃመድ በቀለ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ሠንደቅ ዓላማ ሕዝብን በአንድ ጥላ ስር የሚያሠባሥብ የጋራ ኩራት እና የነጻነት መገለጫ ነው” የሐረሪ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ