“ሠንደቅ ዓላማ ሕዝብን በአንድ ጥላ ስር የሚያሠባሥብ የጋራ ኩራት እና የነጻነት መገለጫ ነው” የሐረሪ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ

9

 

በምሥራቅ አፍሪካ ረጅሙ እና 52 ሜትር በሚረዝም የሠንደቅ ዓላማ መስቀያ ላይ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በሐረር ከተማ በክብር ተሰቅሏል።

ሠንደቅ ዓላማውን የመስቀል ሥነ-ሥርዓት የሐረሪ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች እና የጸጥታ አካላት በተገኙበት ተፈጽሟል።

ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ እንደገለጹት በሐረር ከተማ በከፍታ ቦታ የተተከለው ይህ የሠንደቅ ዓላማ መስቀያ በርዝመቱ በኢትዮጵያ እና በምሥራቅ አፍሪካ 1ኛ ደረጃን የሚይዝ ነው ብለዋል። 72 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው የኢትዮጵያ እና የሐረሪ ክልል ሠንደቅ ዓላማዎች በክብር ተሰቅለውበታል።

ሠንደቅ ዓላማ ሕዝብን በአንድ ጥላ ስር የሚያሠባሥብ የጋራ ኩራት፣ የፓን አፍሪካኒዝም፣ የሉዓላዊነት እና የነፃነት መገለጫ መኾኑን የጠቀሱት ርእሰ መሥተዳድሩ ይህንን እሴት እና የወል ትርክት ለማጠናከር የሠንደቅ ዓላማ ክብር መርሆዎችን ማጉላት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የሠንደቅ ዓላማ መስቀያው በሐረር ከተማ ከባሕር ጠለል በላይ 2900 ሜትር ከፍታ ላይ በሚገኘው የሐኪም ጋራ የተተከለ ነው።

ይህ ግዙፍ መስቀያ በሐረር ከተማ ከሚገኘው “HARAR” ከሚለው የከተማዋ መለያ ስም አጠገብ የተተከለ በመኾኑ የሠንደቅ ዓላማውን እሴት በይበልጥ ጎልቶ እንዲታይ ያደርገዋል ተብሏል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_25_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ።
Next articleየማኅበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድኅን አገልግሎትን ማጠናከር የመሪዎች ቁልፍ ተግባር ሊኾን ይገባል።