
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ዐቢይ አሕመድን (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ2010 ዓ.ም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን ሠርተዋል።
ሀገር በቀል የመደመር የፖለቲካ እሳቤ አዲስ የፖለቲካ ባሕል እንዲኾን አስችለዋል። የጥል ግድግዳ እናፍርስ፤ የፍቅር ድልድይ እንገንባ በሚለው መርሐቸው ለዓመታት ተራርቀው የነበሩ ፖለቲከኞችን አገናኝተዋል። በሥልጣን ዘመናቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በሀገሪቱ ሥልጣን እንዲይዙ እና ሀገር እንዲያገለግሉ አድርገዋል።
በከፍተኛ ችግር ውስጥ የነበረውን የሕዳሴ ግድብ ከችግር በማውጣት እንዲጠናቀቅ አመራር ሰጥተዋል። ከሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ማግስት ታላላቅ ፕሮጄክቶችን አስጀምረዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ አጽፈዋል። ኢትዮጵያን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ብዝኃ ኢኮኖሚ በማሸጋገር አስደናቂ የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖራት አድርገዋል። በከተማ እና በገጠር ኮሪደር ልማቶች የኢትዮጵያን ገጽታ በከፍተኛ ሁኔታ ቀይረዋል።
የኢትዮጵያን ከተሞች ከተጎሳቆሉበት አውጥተው ወደ ውብ እና ሳቢ ገጽታ መልሰዋል። ኢትዮጵያ የስንዴን ምርት ከውጭ መቀበል አቁማ ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሀገር ያደረጓት በእርሳቸው የሥልጣን ዘመን ነው። በሌማት ቱሩፋት መርኃ ግብርም በእንስሳት ሃብት ሀገሪቱ በታሪኳ አይታው የማታውቀውን እድገት እና ለውጥ አምጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸው ታላላቅ ሀገራዊ ሥራዎችን ያሳኩ ዘንድ በድጋሜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ኢትዮጵያን እንዲመሩ ተሹመዋል።
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 
በታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
