
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ከድህነት ለመላቀቅ እና ሉዓላዊነትን ለማጽናት የሕልውና ምሰሶዎች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዓባይ እና ቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ
መኾናቸውን፣ መሻቷም የሕልውና እንጂ የቅንጦት እንዳልኾነ አረጋግጠዋል። ግድቡ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኀይል በማቅረብ ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርና እና ለአገልግሎት ዘርፎች ዕድገት መሠረት በመጣል የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ትንሣኤ እውን ያደርጋል። ለውጭ ምንዛሬ አቅሟ ማደግም
አስተዋጽኦው ከፍ ያለ ነው ማለታቸው የሚታወስ ነው። የባሕር በር ባለቤትነት ደግሞ የውጭ ንግድ ልውውጥን በማቀላጠፍ፣ የትራንስፖርት ወጪን በመቀነስ እና የጂኦፖለቲካዊ ተጽዕኖን በመቋቋም የኢኮኖሚ ነጻነትን የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ፍላጎት ነው። ጥያቄው በአንድ ወደብ ብቻ
መወሰንን በማስቀረት የኢኮኖሚ ስጋትን እና የዋጋ ንረት ጫናን የሚቀንስ ወሳኝ ጉዳይም ነው። የሕዳሴ ግድብ የውስጥ አቅምን አጠናክሮ የማልማት ምልክት ሲኾን የባሕር በር ባለቤትነት ደግሞ ከውጭው ዓለም ጋር የሚደረገውን የንግድ ግንኙነት ነጻ የሚያወጣ ስትራቴጂካዊ
እርምጃ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
