ባለፉት አምስት ዓመታት በሌማት ትሩፋት ምን መሠረታዊ ለውጥ መጣ?

0
የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በዋናነት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና በቤተሰብ ደረጃ የዶሮ፣ የወተት፣ የማር እና የሥጋ ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።
🎙️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሌማት ትሩፋት ማስጀመሪያ እና መገምገሚያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ሌማት ትሩፋት የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እና በቤተሰብ ደረጃ የሀብት ምንጭ ለመፍጠር የተቀየሰ ንቅናቄ እንደኾነ መግለጻቸው ይታወሳል።
“የምግብ ዋስትናችንን በራሳችን ምርት ማረጋገጥ ስንችል የውጭ ምንዛሬን ከመቆጠብ በላይ የዜጎቻችንን ጤና እና ምርታማነት እናረጋግጣለን” ነው ያሉት።
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ዓመታዊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሪፖርት እንደሚያመላክተው በርካታ ወጣቶች በማኅበር እና በግል ተደራጅተው በዶሮ እርባታ፣ ማር በማምረት፣ በከብት፣ በበግ እና በፍየል ማድለብ እና በወተት ሀብት ልማት ዘርፍ ተሰማርተው የራሳቸውን ገቢ ማግኘት ችለዋል።
🚀 አዲስ እየተመሠረተ ያለው መንግሥት የተመዘገቡ የሌማት ትሩፋት ውጤቶችን ለማስቀጠል እና የበለጠ ለማስፋፋት የምርት ጥራት እና የማቀናበሪያ ሰንሰለት መዘርጋት ላይ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የፖሊሲ ምክረ ሐሳብ ይጠቁማል።
የወተት፣ የሥጋ እና የእንቁላል ምርቶችን በስፋት ማቀናበር እና ማሸግ የሚያስችሉ አነስተኛ እና መካከለኛ ፋብሪካዎችን ማስፋፋት እንደሚያስፈለግም አመላክቷል። ፋኦ (FAO) የኢትዮጵያ የግብርና ገበያ ላይ በሠራው ጥናት ደግሞ የገብያ ትስስር፣ ምርት ማቀዝቀዣ እና ማከማቻ መሠረተ ልማት እንደሚያስፈልግ አመላክቷል።
የኢትዮጵያ እንስሳት ሀብት ልማት ኢንስቲትዩትም የመኖ፣ የዝርያ እና አቅርቦት ማሻሻል እንደሚያስፈልግም ገልጿል። የዶሮ እና የከብት መኖ ዋጋ መወደድ አምራቾች ላይ ጫና እያሳደረ በመኾኑ የመኖ አቅርቦትን ማረጋጋት እና ጥራት ያላቸውን ዝርያዎች በስፋት ማቅረብ ያስፈልጋል ብሏል።
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleቴክኖሎጂ ያረቀቀው ሉዓላዊነት:- የኢትዮጵያ የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት የላቀ ሽግግር።
Next article‎ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሀገር በቀል የምርት ሉዓላዊነት