💎 ከምድር ማሕጸን ወደ ሀገር ካዝና፤ የመንግሥት ስልታዊ አቅጣጫ! 💎

4

 

ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ እጅግ ግዙፍ እና አስደናቂ የተፈጥሮ ጸጋን የታደለች ምድር ናት። ወርቅ፣ ኦፓል፣ ታንታለም፣ ሊቲየም፣ እብነበረድ እና የተለያዩ የከበሩ ማዕድናት በምድሯ ማሕጸን ውስጥ በስፋት ይገኛሉ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተተገበሩ የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ለግሉ ዘርፍ የተሰጡ ማበረታቻዎች አጠቃላይ ዘርፉን በአዲስ መነቃቃት ውስጥ ከትተውታል።

በተለይም ጥቁር ገበያን እና ሕገ-ወጥ የማዕድን ዝውውርን ለመግታት በብሔራዊ ባንክ በኩል የተደረጉ የግዢ ዋጋ ማሻሻያዎች አቅራቢዎች ማዕድንን በቀጥታ ወደ ማዕከላዊ ካዝና እንዲያስረክቡ በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን በእጅጉ አሳድገውታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እንደገለጹት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በምታከናውናቸው ተግባራት ከድህነት ሰንሰለት ተላቅቃ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ አጠናክራ ቀጥላለች፤ ከእነዚህ ዘርፎች መካከልም ለማዕድን ሃብት የተሰጠው ትኩረት አንዱ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ዘርፉን በዕውቀት እና በሀገር በቀል እምቅ አቅም እያሳደጉ መሄድ እንደሚገባም አንስተው ነበር። የነገዋን ኢትዮጵያ በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሃብት ስለመኾኑም በተደጋጋሚ ሲያነሱ ተስተውለዋል።

ዛሬ ላይ ቱሪዝም፣ ግብርና እና ኢንዱስትሪው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሞተር እያነቃቁ እንዳሉት ሁሉ የማዕድን ዘርፉም የኢትዮጵያ ቀጣይ ትልቅ የዕድገት ተስፋ ተደርጎ እየተወሰደ ይገኛል።

አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩት ግዙፍ የልማት ንቅናቄዎች እና የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች በዘርፉ ላይ ለተሰማሩ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች እኩል እና ፍትሐዊ የንግድ መደላድል ፈጥረዋል።

ይህ ስትራቴጂካዊ ዘርፍ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦትን እና ኤክስፖርትን በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩ ባለፈ በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ አያሌ ወጣቶች አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር እና የቴክኖሎጂ ክህሎትን በማጋራት ረገድ የሚጫወተው ሚና የጎላ ነው።

ኢትዮጵያ የታቀደውን የብልጽግና ርዕይ በተጨባጭ ምድር ላይ እውን ማድረግ የምትችለው የየዕለቱን የልማት አሻራዎች በማጠናከር ነው። የማዕድን ሃብቱን ለሀገር ግንባታ ዋነኛ ዓምድ አድርጎ የመጠቀም ሥራም አዲስ በተመሠረተው መንግሥት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#አሚኮ #የማዕድን_ልማት​ #ኢትዮጵያ

#ባሕር_ዳር #መስከረም_25_2019_ዓ_ም

በሰለሞን አንዳርጌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“በእኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ልመና ታቆማለች፤ የባከኑ ሀብቶቿ ይወጣሉ”
Next articleኢትዮጵያ ሉአላዊነቷን፣ የግዛት አንድነቷን እና ብሔራዊ ፍላጎቶቿን ለማስከበር ዝግጁ ናት።