በአምራች ኢንዱስትሪው የተገኘው አስደናቂ ስኬት !

10

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣት እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሠጥቶ ተሠርቷል። የፖሊሲ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ የተቋም ግንባታ እና አደረጃጀት ሥራዎች በስፋት ተሠርተዋል።

ለኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ የኾኑ አምስት የልማት ዘርፎች ተለይተውም ልዩ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ስኬታማ ለውጦች ተመዝግበዋል። ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ከአምስቱ የልማት መሰሶዎች መካከል አምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አንዱ ነው።

ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በሀገሪቱ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት፤ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በሚያስችል መልኩ ትኩረት ተሰጥቶት ሢሠራ ቆይቷል።

በዘርፉ ዕድገት ለማምጣት በተደረገው የፖሊሲ ለውጥ፤ የመዋቅራዊ ማሻሻያ እና ልዩ የአመራር ክትትል የአምራች ኢንዱስትሪውን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል። ለአብነትም:-

👉 በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መርሐ ግብር በዘርፉ የሚታዩትን የመልካም አሥተዳደር፣ የኃይል፣ የፋይናንስ እና የግብዓት አቅርቦት ችግሮችን መፍታት ተችሏል።

👉 በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢንቨስትመንት ማነቆዎችን በመፍታት የግል ባለሃብቶች በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያሳድጉ ተደርጓል።

👉 በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተቀናጁ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ሙሉ ሥራ በማስገባት እና ከአርሶ አደሮች ጋር በማጣመር የገበያ ትስስር መፈጠር ተችሏል።

👉የፉብሪካ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን የሚያስችል አሠራር በመዘርጋት በራስ አቅም ለማምረት ጥረት ተደርጓል።

በተወሰዱት ሀገራዊ እርምጃዎች ተስፋ ሰጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

👉 ተዘግተው የነበሩ በርካታ ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል። በዚህም 47 በመቶ የነበረው የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 67 በመቶ ደርሷል።

👉 የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ቁጥር ከ8 ሺህ ወደ 26 ሺህ አድጓል። ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ከ3 ሺህ ወደ 4ሺህ 200 ደርሰዋል።

👉የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት እድገት በ2018 በጀት ዓመት ብቻ 22 ነጥብ 7 በመቶ አድጓል። በበጀት ዓመቱ ብቻ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ተችሏል።

👉 አጠቃላይ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 20 ነጥብ 3 በመቶ ማሳደግ እንደተቻለ ተመላክቷል።

በአነስተኛ፣ በመካከለኛ እና በከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች በየዓመቱ በ100 ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_25_2019_ዓ_ም

✍️በአሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleከደካማ እንቅስቃሴዎች ወደ ቢሊዮን ዶላሮች የተሸጋገረው የኢትዮጵያ የቱሪዝም
Next article“በእኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ልመና ታቆማለች፤ የባከኑ ሀብቶቿ ይወጣሉ”