የኢትዮጵያውያን የሥነ መንግሥት እሳቤ እስከምን ድረስ ነው?

9
ኢትዮጵያ ዓለም ከሥልጣኔ ርቃ በነበረበት በዚያ ዘመን ሳይቀር ሥርዓተ መንግሥት ያላቸው ሕዝቦች መኖሪያ እንደነበረች ታሪክ ያስረዳል።
የአማራው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኦሮሞው አባ ገዳ፣ የሶማሌ ኡጋሶች፣ የደቡብ ባለለምለም ጨፌ የተከበሩ አባቶች ለኢትዮጵያ የዳበረ የሥነ መንግሥት ልምድ እርሾዎች ናቸው።
ዓለም ገና ስለዴሞክራሲ እና የሰው ልጆች መብት ማውራት ሳይጀምር ኢትዮጵያ ግን በሀገር በቀል ጥንተ የሥነ መንግሥት ዕውቀቶች ሕዝብን ስታስማማ፤ ሀገረ መንግሥትም ስታጸና ኖራለች።
ዛሬም ሀገረ መንግሥት ለማጽናት ቀናኢ የኾነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈተናዎችን አልፎ እና ካርዱን ተጠቅሞ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመትከል ታትሯል። “አትመርጥም” ተብሎ ቢተኮስበት እንኳን ፈተናዎችን እየበጣጠሰ አልፎ “እምቢ መንግሥቴን የማጸናው በካርዴ ነው” በማለት ምርጫውን አካሄዷል።
ዛሬ መሥከረም 25/2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያውያን ልዩ ቀን ናት። የከበዱ የሚመስሉ ፈተናዎች በሕዝብ እንደአለት የጠነከሩ ብርቱ ፍላጎቶች ታልፈው የተመረጠ መንግሥት የሚቋቋምበት ቀን ነው።
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹
በአሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየኢትዮጵያ ታላቅ የድል ብስራት ቀን!
Next articleጠንካራ ተቋማት ሀገርን ተሸክመው የሚቆሙ መሠረቶች ናቸው።