የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችን እና ምክረ ሃሳቦችን አስረከበ።

28

 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችን እና ምክረ ሃሳቦችን አስረክቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በተካሄደ መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችን እና ምክረ ሐሳቦችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት ዛሬ በይፋ አስረክቧል።
‎
‎ይህ የሰነድ ርክክብ፤ በምክክር እና በሰላማዊ መንገድ የኢትዮጵያን የቆዩ ሀገራዊ ፈተናዎች መፍታት አስፈላጊ መኾኑን በመገንዘብ፤ በመደመር መንግሥት ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ የተበጀለትን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አንድ ትልቅ ምዕራፍ ያበስራል። ሂደቱ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ስምምነትን ለመፍጠር የሚያስችል አካታች መድረክ መሥርቷል።
‎
‎ባለፉት አራት ዓመታትም ይህ ሂደት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ማሳተፍ ችሏል። ተሳታፊዎች ባደረጓቸው ሰፊ ምክክሮች እና በተጠናቀቀው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አማካኝነት እይታዎቻቸውን ለማንጸባረቅ፣ ልዩ ልዩ አመለካከቶችን ለመስማት እና የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን መስኮች ለመለየት ዕድል አግኝተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው
የእነዚህ ውጤቶች በይፋ መቅረብ በምክክሩ የተሰበሰቡ እይታዎችን እና የውሳኔ ሐሳቦችን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማሸጋገር የተቀየሰ ትልቅ እርምጃ ነው።

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!

#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም

‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous articleየሥነ-ሥርዓት ሕጉን በትክክል መተግበር ለፍትሕ አሥተዳደሩ ውጤታማነት ወሳኝ ነው።
Next article“የአጀንዳ ርክክቡ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሀገራዊ ፈተናዎች በሰላማዊ ምክክር ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)