
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በምክክር የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች አስረክቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል መንግሥት እና ለክልል መንግሥታት በይፋ ርክክብ የተደረገበትን መርሐ ግብር ዛሬ ተከታትያለሁ ነው ያሉት።
ይህ የሰነድ ርክክብ ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ የሚያስመዘግብ ነው፤ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሀገራዊ ፈተናዎች አካታች በኾነ ውይይት፣ በሰላማዊ ምክክር እና በራሳችን ሀገር በቀል የመፍትሔ አምጭ እሴቶች ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!
#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
