ከተሳሳተ የትግል መንገድ ወደ ሰላም አርበኝነት።

6

 

የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰላም አማራጭን የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ለመመለስ እና የሰላም አርበኛ ለማድረግ ሲሰጥ የቆየውን ሥልጠና አጠናቅቋል።

አሚኮ ያነጋገራቸው የቀድሞ ታጣቂዎች እንደገለጹት የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ በሚል የተጀመረው የተሳሳተ ትግል አሁን ላይ የግለሰቦችን እና የውጭ ጠላቶችን ፍላጎት ማሳኪያ ኾኗል።

ቀደም ሲል ሕዝቡን ሲጨቁኑ ከነበሩ ሀገር-ጠል ኀይሎች ጋር ጥምረት መፈጠሩ ቀድሞውንም ቢኾ የተሳሳተ መንገድ መኾኑ እና የግል ፍላጎት ማሳደጃ መኾኑን ያሳያል ብለዋል። ሂደቱ ሕዝቡን ለከፋ ጉስቁልና ከመዳረጉ ባሻገር በርካቶችን ላላስፈላጊ መስዋዕትነት መዳረጉን ጠቁመዋል።

ከባለፈው ስህተታቸው በመፀፀት አሁን ላይ ለዞኑ ዘላቂ ሰላም የበኩላቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መኾናቸውን ገልጸዋል። ሌሎች በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎችም የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር አዱኛ አዳሙ መንግሥት ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ያከናወናቸው ተግባራት አዎንታዊ ውጤት እያስገኙ መኾናቸውን ተናግረዋል።

አሁንም ለሰላም ጥሪው በሩ ክፍት መኾኑን የጠቀሱት ኀላፊው ሰላማዊ አማራጭን በማይቀበሉት ላይ ግን የመንግሥት የሕግ ማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!

#አሚኮ #ሰላም_አማራክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹​

#ፍኖተ_ሰላም #መስከረም_23_2019_ዓ_ም

‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“በርካታ ሰዎች በሚገኙባቸው ስብሰባዎች ላይ በጋራ ደም መለገስ የበርካታ ወገኖችን ሕይወት ይታደጋል”
Next articleለሕዝባችን የገባነውን ቃል ለመፈጸም ታሪካዊ ኃላፊነታችንን እንወጣለን!