“በርካታ ሰዎች በሚገኙባቸው ስብሰባዎች ላይ በጋራ ደም መለገስ የበርካታ ወገኖችን ሕይወት ይታደጋል”

8

 

በሁለተኛው የአማራ ክልል ዳኞች ጉባኤ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መሪዎች ደም ለግሰዋል።

ደም ከለገሱት መሪዎች መካከል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው ከ2 ሺህ በላይ ዳኞች በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ ሲኾን ጎን ለጎንም ደም በመለገስ የወገን አለኝታነታቸውን እየገለጹ ነው ብለዋል። “ደም መስጠት የሰዎችን ሕይወት ማዳን ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ በእንዲህ አይነት ጉባኤዎች እና በማንኛውም ስብሰባዎች ሰዎች ሲገናኙ ደም መለገስ ባሕል መኾን እንዳለበት ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከባሕር ዳር ደም ባንክ ጋር በመነጋገር በ2018 ዓ.ም የዳኞች ጉባኤ ላይም በአንድ ጊዜ የተለገሰ እና በብዛቱ ሪከርድ የነበረ ተሳትፎ መደረጉን አስታውሰዋል።

ደም መለገስ የጤና በረከት እንጅ ችግር እንደሌለው በሕክምና ይመከራል። በርካታ ሰዎች የሚገኙበት ጉባኤ ሲታቀድ ደም መለገስም አብሮ ታስቦ እና ፕሮግራም ተይዞለት ቢሠራበት በደም እጦት የሚቸገሩ ወገኖችን በዘላቂነት መታደግ እንደሚቻልም ፕሬዝዳንቱ ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

ደም የለገሱ ዳኞች ደም መለገስ ሕይወትን ማዳን ነው፤ ለራስም ጤና ነው ብለዋል። የሰዎችን የመኖር ተስፋ ከመመለስ በላይ ደስታ የለም፤ ቢቀነስብን ጉዳት የሌለውን ደም በመለገስ የወገን አለኝታነትን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

ደም በዘመቻ ብቻ ሳይኾን ግለሰቦች ፕሮግራም ይዘው በየጊዜው ሊለግሱት የሚገባ ሰብዓዊ ስጦታ ስለመኾኑም ተናግረዋል። የዜግነት እና የሕዝብ ፍቅር አንዱ ማሳያ ስለመኾኑም ደም ለጋሾች አንስተዋል።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹

#አሚኮ #donateblood #Ethiopia🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article‎ዛሬ ግንባታው የተጀመረው አዳሪ ትምህርት ቤት ለነገው ትውልድ መሠረት የሚጥል ነው።
Next articleከተሳሳተ የትግል መንገድ ወደ ሰላም አርበኝነት።