‎”ሕዝቡ ለሀገር ሰላም ዘብ እንዲኾን እንሠራለን ፤ ስለ ሰላምም እንጸልያለን”

7

‎‎
‎የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ሥራዎች ዙሪያ በከተማው ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።
‎
‎የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞላ ሁሴን ሀገሪቱ ሰላሟን አስጠብቃ ልማቷን እያስቀጠለች መኾኑን ገልጸዋል።

ማኅበረሰቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ መሠራቱንም አንስተዋል። ነገር ግን ሰላምን ለማደፍረስ እና ልማትን ለማደናቀፍ የሚጥሩ አካላትን ወደ ጎን በመተው ዘላቂ ሰላምን ማጽናት ይገባል ብለዋል።
‎
‎ማኅበረሰቡ በጋራ ኾኖ የተጀመረውን የልማት እና የሰላም ተስፋ ማስቀጠል እንዳለበትም አንስተዋል። በተለይም የሃይማኖት አባቶች ስለ ፍቅር እና ስለ ሰላም በመስበክ እና በማስተማር የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
‎
‎የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኀላፊ አሸናፊ አግማስ የሃይማኖት አባቶች ለሀገር ሰላም ድርሻቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል። በሥራቸው ያለውን የሃይማኖት ተከታይ አንድነቱን እንዲያጠናክር በማድረግ እና ስለ ሰላም በማስተማር የበኩላቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል።
‎
‎በውይይቱ የተሳተፉ የሃይማኖት አባቶችም የሀገርን ሰላም በዘላቂነት ለማጽናት አንደሚሠሩ ተናግረዋል። በተለይም ወጣቱን በመልካም ሥነ ምግባር እንዲያደግ እና መልካም እሴቶችን እንዲቀጥሉ ለማድረግ በየ ሃይማኖታቸው እንደሚሠሩ ነው የገለጹት።
‎
‎”ሕዝቡ ለሀገር ሰላም ዘብ እንዲኾን እንሠራለን” ስለ ሰላምም እንጸልያለን” ብለዋል።
‎
‎ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹
‎
‎#አሚኮ #ሰላም #ኢትዮጵያ🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም
‎
‎ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየትምህርት ሚኒስቴር በባሕር ዳር ከተማ የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀመረ።
Next article‎የነዋሪዎቿ ሰላም ወዳድነት ደብረ ብርሃንን በልማት ግንባር ቀደም አድርጓታል።