
በአፍሪካ ቀንድ የቀጣናውን ልማት፣ ሰላም እና አብሮነት በጋራ ማፋጠን በሚገባበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የኤርትራ መንግሥት ግን ከተበላሸው የትላንት ታሪካዊ አካሄዱ ሳይታረም ዛሬም የሴራ ፖለቲካውን ከመዘርጋት አልተቆጠበም።
ኤርትራ ኢትዮጵያ ጠንካራ፣ ሉዓላዊነቷ የተከበረ፣ አንድነቷ የተጠበቀ እና በኢኮኖሚ የበለጸገች ሀገር ኾና እንድትቀጥል አትፈልግም።
ይህንኑ እኩይ ዓላማዋን ለማሳካትም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በተለይም እንደ ግብጽ ካሉ ወገኖች ጋር ያልተቀደሰ ጥምረት በመፍጠር ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲ እና በኢኮኖሚ ለማግለል እንዲሁም ማዕከላዊ አቅሟን ለማዳከም ቀን ከሌት እየሠራች ትገኛለች።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድኖችን በመሳሪያ፣ በፋይናንስ እና በሥልጠና በመደገፍ የሀገሪቱን የውስጥ ሰላም ለማደፍረስ እየሠራችም ነው።
ኢትዮጵያ የባሕር በርን በሰላማዊ መንገድ እና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት እንደ ግዛት ሉዓላዊነት ጥሰት በመቁጠር የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዋን በበጎ ጎን ከመመልከት ይልቅ ፍፁም ተቃውሞን እያንጸባረቀች ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ በቀጣናው የምትፈልገው ሰላም እና የጋራ ልማት እንጂ ጦርነት እንዳልኾነ አጽንኦት መስጠታቸው ይታወሳል። ኾኖም ግን የሀገርን ሉዓላዊነት እና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውም ጥቃት ከተቃጣ መንግሥት በፍጹም እንደማይታገስም ገልጸዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሐኑ ጁላ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ከየትኛውም ወገን የሚሰነዘርን ድንበር ተሻጋሪ ስጋት እና ጥቃት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመመከት ሁልጊዜ በሙሉ ብቃት እና ዝግጁነት እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!
#አሚኮ #የኤርትራ_ጸረሰላም_አካሄድ #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
