የኢሬቻ በዓል እየተከበረ ነው።

11

 

ኢሬቻ የክረምቱን መውጣት ተከትሎ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የሚከበር የምስጋና በዓል ነው።

በዓሉ በጠሩ ወንዞች ዙሪያ ለምለም ጨፌ ተይዞ በአንድነት የሚከወን የምስጋና፣ የፍቅር እና የይቅርታ መድረክም ነው።

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓልም በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮሞ ሕዝብ በተጨማሪ የሌሎችም ወንድምና እህት ሕዝቦች ተወካዮች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉ አከባበር በጠዋቱ በአባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ምርቃት ተጀምሯል።

#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!

#አሚኮ #ኢሬቻ #Ethiopia

Previous articleውብ ሀገሬ… በአንቺ እኮ ነው መከበሬ”
Next article🇪🇹 የግብጽ እና ኤርትራ የዓባይን ጸጋ እና የቀይ ባሕርን ራዕይ የማደናቀፍ ጂኦ-ፖለቲካዊ ሴራ