በዲጂታል ኢኮኖሚው የሴቶችን ተሳታፊነት የሚያሳድግ መርሐግብር በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ።

1
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው “የአፍሪካ ሴት ልጆች የቴክኖሎጂ ኢንሼቲቭ” ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።
የመርሐግብሩ ሥራ አሥኪያጅ አሚን አየለ እንዳሉት መርሐግብሩ የሴቶችን ተፎካካሪነት በመጨመር በዲጂታል ኢኮኖሚው ውስጥ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
የ4ኛ ዓመት የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪ ቃልኪዳን ታመነ በዘርፉ አሁንም ድረስ የሚታየውን የመሠረታዊ አስተሳሰብ ክፍተት ለመቅረፍ አዲሱ የቴክኖሎጂ ማዕከል ለሴት ተማሪዎች ያለው ጠቀሜታ የጎላ መኾኑን ገልጻለች።
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስማረ መለሰ (ዶ.ር) ማዕከሉ ያገኘው ጥራት ያለው የኮምፒውተር ድጋፍ የምርምር እና የመማር ማስተማር ሂደቱን በእጅጉ እንደሚያቀላጥፈው ጠቅሰው፣ ድጋፉን በአግባቡ በመጠቀም የሴት ተማሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ሥራ አሥፈጻሚ ስዩም መንገሻ በበኩላቸው “ዲጂታል ኢትዮጵያን” እውን ለማድረግ በአስተሳሰብ ለውጥ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበው ለሥራው ውጤታማነት አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
✍️ዘጋቢ፦ዮናስ ታደሰ
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሴራ በፅናት ከማክሸፍ ባለፈ በሉዓላዊነቷ አትደራደርም” ዶ/ር ግዛቸው አስራት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተመራማሪ
Next articleየአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል።