
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ከተማዋን ጽዱ፣ ውብ እና ለነዋሪዎች የተመቸች የሚያደርጉ መኾናቸውን ገልጸዋል።
የሕዝብ እና የመንግሥት ትብብር የታየባቸው ፕሮጄክቶች መኾናቸውንም አመላክተዋል። የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በጥራት የተገነባ እና ለደብረ ብርሃን ልዩ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል። ደብረ ብርሃን እና ሰሜን ሸዋ ምርታማ የኾነ ለእድገት ከፍተኛ ዕድል ያለው መኾኑንም አመላክተዋል።
ደብረ ብርሃን ልዩ ዕድል ላይ የምትገኝ ከተማ ናት ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ሰሜን ሸዋ ልዩ ጸጋ እና ዕድል ያለው መኾኑን ነው የተናገሩት። ባለሃብቶች የሚፈልጉት አካባቢ መኾኑንም አንስተዋል። ደብረ ብርሃን ከተማ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የሚያስፈልጋት መኾኗንም ገልጸዋል። የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን በመገንባት የሕዝብ አገልግሎት እርካታን ማረጋገጥ እና በሕዝብ ዘንድ የሚነሳውን የአገልግሎት ቅሬታ መፍታት እንደሚገባም አመላክተዋል።
የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣን እና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል። ተገልጋዮች በአግባቡ መገልገል፣ አገልጋዮች ደግሞ አስፈላጊውን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው አመላክተዋል። መሶብ ውጤታማ የሚኾነው አምሮ በመገንባቱ ብቻ ሳይኾን ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ሲሰጥበት ነው ብለዋል።
ልማትን የሚያመጣ ሥራ መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት ለደብረ ብርሃን እና ለሰሜን ሸዋ ዞን ልማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
#የመደመር_መንግሥት
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_22_2019_ዓ_ም
✍️ ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
