🌾የአርሶ አደር ሠርቶ ማሳያዎች – ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለምርት እድገት ምሶሶዎች

1

 

ምርታማነትን በማሳደግ ዘመናዊ የግብርና አሠራርን ተግባራዊ ለማድረግ የአርሶ አደር ሠርቶ ማሳያዎች ድርሻቸው ከፍተኛ ነው።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች እንደሚሉት
ከሠርቶ ማሳያዎች በተግባር የገበዩትን ዕውቀት በማሳቸው ላይ ተግባራዊ በማድርግ ምርታማነታቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ነግረውናል። ይህም ትልቅ የምርት ትምህርት ቤት ነው ይላሉ።

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ጥላሁን ንጋቱ ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሮችን በተግባር የተደገፈ ግንዛቤ ለመፍጠር ሠርቶ ማሳያዎችን በአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከላት እና በማሳቸው ላይ ተግባራዊ በማድረግ ትልቅ ማስተማሪያ ኾኖ እያገለገለ ነው ብለዋል። ይህም ሥራ ምርታማነትን በማሳደግ እና የምርት ጥራትን በመጠበቅ ለውጥ በማምጣት የአርሶ አደሮችን የኑሮ ደረጃ እያሻሻለ ይገኛል ነው ያሉት።

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ቀኝአዝማች መሥፍን እንደገለጹ ሰርቶ ማሳያ አርሶ አደሮች ግንዛቤያቸውን፣ ዕውቀታቸውን እና ክህሎታቸውን ወደ ተግባር በመቀየር ትልቅ የኤክስቴንሽን ዘዴ ነው። በተለይም አርሶ አደሮችን በማንቃት እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት እንዲጠቀሙ በማድረግ ለምርት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል ነው ብለዋል።

​ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት አርሶ አደሮች በንድፈ ሃሳብ ከሚነገሩ ሃሳቦች ይልቅ፣ ከአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከላት፣ ከሞዴል አርሶ አደሮች ማሳዎች እና ከምርምር ማዕከላት የሚወጡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና አሠራሮችን በተግባር ሠርቶ ማሳየት በፍጥነት ወደ ተግባር የሚቀይር ነው። አዳዲስ የሰብል ዝርያዎች ሲወጡም አርሶ አደሮች በቀጥታ ሳይወስዳቸው በሠርቶ ማሳያዎች አሳይቶ በሠፊው እንዲተገብሩ ማድረግ ለዘላቂ የቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ ዋስትና ነው ብለዋል።

አርሶ አደሩ በሜዳ ላይ በተግባር እየተመለከተ አመለካከቱን የሚቀይርበት ሰበካ ሳይኾን የተግባር ሂደት፣ በምርታማነትና በምርት እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣ መኾኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት። የአርሶ አደር ሰርቶ ማሳያዎች በምርምር፣ በግብርና ኤክስቴንሽን እና በአርሶ አደሮች መካከል ወሳኝ ድልድይ ነውም ብለዋል።

ሠርቶ ማሳያዎች ምርታማነትን በማሳደግ የግብርና ቴክኖሎጂን በዘላቂነት በመገንባት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ትልቅ አስተማማኝ ዋስትና መኾኑም ተመላክቷል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_22_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleሁሌም ከጠላቶቿ በላይ የምትውለው ታላቋ ኢትዮጵያ!🇪🇹
Next article“ደብረ ብርሃን ልዩ ዕድል ላይ የምትገኝ ከተማ ናት” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ