የቀደመ ስልት እስረኞች፤ የግብጽ ሴራ እና የማይበገረው የኢትዮጵያ ጽናት!

3
ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለው የውጭ ፖሊሲ ኢትዮጵያን በማዳከም ላይ የተመሠረተ ነው። ኢትዮጵያን በወታደራዊ፣ በዲፕሎማሲያዊ እና በውስጥ ግጭት በማዳከም ዓባይን በብቸኝነት ተቆጣጥራ መጠቀም ደካማ መርሕ እና አቋሟ ነው።
በቀጥታ ወረራ ፈጽማ ኢትዮጵያን በጦርነት ማሸነፍ ያልቻለችው ግብጽ ስልቷን ቀይራ ውስጣዊ አንድነትን ማዳከም የዓላማዋ ማስፈጸሚያ ስትራቴጅ አድርጋ ትጠቀማለች።
በሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ ጥናቶች ውስጥ “ግብጽ እና የዓባይ ፖለቲካ (ዳንኤል ኪዳኔ:1999)” በሚል ርዕስ የታተመው ጥናትም ይህንኑ ያረጋግጣል።
“ኢትዮጵያ ስትዳክም እና በውስጥ ስትከፋፈል ግብጽ እረፍት ታገኛለች። ነገር ግን ኢትዮጵያ ስትበለጽግ፣ በራሷ ስትተማመን እና ቀጣናው ውስጥ መሪ ሚና ስትጫወት ግብጽ ትጨነቃለች” በማለት ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን የውጭ ፖሊሲ እና ጠላትነት በግልጽ ይተነትናል።📖
በተለያዩ ዘመናት የአማጺ ቡድኖችን በማደራጀት እና መደገፍ የትርምስ እቅዶችን በመንደፍ በኢትዮጵያ ላይ ጥቅሟን የማስከበር ምኞቷን እውን ለማድረግ ጥራለች፤ ዛሬም ቀጥላበታለች።
​⚠️ዛሬም የሻብያን እና የሕወሃትን በመጠቀም ኢትዮጵያን በውክልና ጦርነት በማዳከም ፍላጎቷን ለማሳካት እየጣረች ትገኛለች። ነገር ግን ኢትዮጵያ በየዘመናት የሚያጋጥሟት ጠላቶችን እያሳፈረች እንደመለሰቻቸው ሁሉ ዛሬም በሉዓላዊነቷ የማትደራደር ሀገር ናት። ለዚህም ዓለም መስክሮላታል።
ግብጽን በጉንደት እና ጉራ፣ ደርቡሽን በኩፊት ያሸነፈው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገር ሉዓላዊነት በሚመጣ ኀይል እንደማይደራደር የሚያረጋግጡ አብነት የታሪክ ምስክሮች ናቸው።​
ኢትዮጵያ ዛሬም ይህንን የብሔራዊ አርበኝነት የሚያስቀጥል ትውልድ ያላት ሀገር መኾኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አሰገንዝበዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ማንም ጣልቃ እንዲገባ ዕድል አንሰጥም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ጠላቶች ስሌት ኢትዮጵያ ድልብ ሃብት፣ የማይገዛ ሕዝብ፣ የማትደፈር ሀገር መኾኗን በመካድ የሚመጡ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ጠላቶች ለቀደመ ስልት እስረኛ በመኾን ኢትዮጵያን የማንበርከክ ከንቱ ምኞት ላይ የተመሠረተ ስልት ስለመኾኑም ጠቁመዋል።
ለዘመናት በቀጥታ ወረራ ሞክረው መሸነፋቸውን የካዱት ግብጾች እና መሰሎቿ ዛሬም በኢትዮጵያ ላይ ዳግም መነሳታቸው ከንቱ ምኞት ስለመኾኑም ተናግረዋል።
✍️በአሰፋ ልጥገበው
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleሴራዎችን እየበጣጠሰች በመቆም የቀጣናው አለኝታነቷን የምታበስረው ኢትዮጵያ!
Next articleየግብጽ ሴራ እና የኢትዮጵያ ጽናት